Co-authored-by: whatzittoya <whosendall.com> Co-authored-by: Roshan Jossy <roshanjossey@gmail.com>
7.1 KiB
የመጀመሪያ አስተዋጽዖዎች
ይህ ፕሮጀክት ጀማሪዎች የመጀመሪያ አስተዋጾ የሚያደርጉበትን መንገድ ለማቅለል እና ለመምራት ያለመ ነው። የመጀመሪያዎን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከፈለጉ ከታች ያሉትን ደረጃዎች ይከተሉ
command line ካልተመቸህ, GUI መሳሪያዎችን በመጠቀም አጋዥ ስልጠናዎች አሉ።.
በማሽንዎ ላይ git ከሌለዎት, ይጫኑት.
Fork this repository
በዚህ ገጽ ላይኛው ክፍል ላይ ያለውን fork ቁልፍን ጠቅ በማድረግ ይህንን ይጫኑት። ይህ በአንተ መለያ ውስጥ የዚህን repository ቅጂ ይፈጥራል።
Clone the repository
አሁን Fork ይህን repository ወደ ማሽንዎ. ወደ GitHub መለያዎ ይሂዱ, የእርሶን repository ይክፈቱ. የኮድ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ እና ከዚያ ቅጂውን ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ ለመቅዳት.
git clone "የቀዱትን url' ያስገቡ"
"የቀዱትን url' ያስገቡ" (ያለ ጥቅስ ምልክቶች) ይህ የዚህ repository url ነው(የእርሶ ቅጂ ፕሮጀክት). url ለማግኘት የቀደመውን ደረጃዎች ይመልከቱ.
ለምሳሌ:
git clone https://github.com/this-is-you/first-contributions.git
where this-is-you የእርስዎ GitHub መለያ ስም ነው።. እዚህ በ GitHub ላይ ያለውን የመጀመሪያ አስተዋፅዖ repository ይዘቶችን ወደ ኮምፒውተርዎ እየገለበጡ ነው።
Create a branch(ቅርንጫፍ ይፍጠሩ)
በኮምፒተርዎ ላይ ያለውን repository ማውጫ ይቀይሩ (እዚያ ከሌለዎት):
cd first-contributions
አሁን የ git checkout ትዕዛዝን በመጠቀም ቅርንጫፍ ይፍጠሩ:
git checkout -b <add-your-new-branch-name>
ለምሳሌ:
git checkout -b github-ethiopia
አስፈላጊ ለውጦችን ያድርጉ እና ለውጦችን commit ያድርጉ
አሁን የ Contributors.md ፋይልን በጽሑፍ አርታኢ(editor) ውስጥ ይክፈቱ፣ ስምዎን በእሱ ላይ ያክሉ። በፋይሉ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ አይጨምሩት። በመካከል የትኛውም ቦታ ላይ ያስቀምጡት. አሁን, ፋይሉን ያስቀምጡ(save).
ወደ የፕሮጀክት ማውጫው ሄደው የ git status ከፈጸሙ ለውጦች እንዳሉ ያያሉ።
የ git add ትእዛዝን በመጠቀም እነዚያን ለውጦች አሁን በፈጠሩት ቅርንጫፍ ላይ አክል፡
git add Contributors.md
አሁን የ git commit ትዕዛዝ በመጠቀም እነዚህን ለውጦች ያድርጉ፡
git commit -m "Add <የእርስዎ-ስም> to Contributors list"
<የእርስዎ-ስም> ፋንታ የራስዎትን ስም ይጻፉ.
ለውጦችን ወደ GitHub ይጫኑ
git push የሚለውን ትዕዛዝ በመጠቀም ለውጦችዎን ይጫኑ
git push origin <የእርስዎ-branch-name>
<የእርስዎ-branch-name> ፋንታ የራስዎትን branch ስም ያስገቡ
ለውጦችዎን ለግምገማ ያስገቡ
በ GitHub ላይ ወደ repository ከሄዱ፣ Compare & pull request ጥያቄን ያያሉ። በዚያ ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
አሁን pull request ጥያቄውን ያስገቡ
በቅርቡ ሁሉንም ለውጦችዎን ወደ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ቅርንጫፍ አዋህዳለሁ. ለውጦቹ ከተዋሃዱ በኋላ የማሳወቂያ ኢሜይል ይደርስዎታል።
ከዚህ ወዴት መሄድ አለብዎት ?
እንኳን ደስ ያለህ! አሁን መደበኛ fork -> clone -> edit -> pull request ሂደትን ጨርሰዋል. እንደ አስተዋጽዖ አበርካች ብዙ ጊዜ ይህ ሂደት ያጋትሞታል
አስተዋጾዎን ያክብሩ እና ለጓደኞችዎ እና ተከታዮችዎ ያካፍሉ ወደ ዲህረ ገጾ በመሄድ.
ማንኛውም እርዳታ ከፈለጉ ወይም ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የእኛን Slack ቡድን መቀላቀል ይችላሉ.
አሁን ለሌሎች ፕሮጀክቶች በማበርከት እንጀምር. እርስዎ ሊጀምሩባቸው የሚችሉ ቀላል ጉዳዮች ያላቸውን የፕሮጀክቶች ዝርዝር አዘጋጅተናል።. እኚህን ማስፈተሪያ ይከተሉ.
ተጨማሪ ቁሳቁስ
ሌሎች መሳሪያዎችን በመጠቀም አጋዥ ስልጠናዎች
| GitHub Desktop | Visual Studio 2017 | GitKraken |
